Monday 24 November 2014

Hiber Radio: የአቶ ግርማ ሰይፉ ንግግር የአንድነት አቋም አይደለም ሲሉ አቶ በላይ ፈቃዱ ተናገሩ * ከለንደን ሶሪያ ሄዶ አሸባሪዎችን የተቀላቀለ አንድ ሀበሻ ተገደለ


ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ህብር ሬዲዮ ህዳር 14 ቀን 2007 ፕሮግራም !
<... በእስር ላይ በሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ ሕዝቡ ማወቅ አለበት...በጸረ ሽብር ሕጉ የሚወነጀሉ ላይ የሚቀርበውን ክስ አንቀበለውም :: እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ የኦነግ አባላት ቦንብ አፈነዱ ተብሎ ያ ድርጊት ግን በስርዓቱ የደህነት ሰዎች ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን ዊክሊክስ አጋልጧል እነሱ ግፍ እየፈጸሙ የሚያናግሩትን አንቀበልም...አቶ ግርማ ከዚህ ቀደም አንዷለም ግንቦት ሰባት ከሆነ እኔም ግንቦት ሰባት ነኝ ማለት ነው በሚል ነው እስሩን የተቃወመው ። አሁን የተናገረው ግን የራሱ እንጂ የአንድነት አቋም አይደለም። መጠንቀቅ ያለብን ግን...>
የአንድነት ፕሬዝዳንት አቶ በላይ ፈቃዱ ሰሞኑን አንድነት የጀመረውን ዘመቻ፣ አቶ ግርማ ሰይፉ በተናገሩት ላይ፣ በምርጫውና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)
የኦባማ ኬር ዳግም ምዝገባና የአይ ኤር .ኤስ ቅታት ባልተመዘገቡት ላይ (ልዩ ቃለ መጠይቅ ከአቶ ተካ ከለለ በአትላንታ የቲኬ ሾው አዘጋጅ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ )
የአሜሪካ የምስጋና ቀንና የፕሬዝዳንቶቹ የምህረት ተግባር( ልዩ ዝግጅት ስለ ምስጋና ቀን)
ሌሎችም ዜናዎቻችን
አልሸባብ በኢትዮ ኬኒያ ድንበር ኦነግ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ 28 ሙስሊም ያልሆኑ ሰላማዊ ሰዎችን ረሸነ።
ከለንደን ሶሪያ ሄዶ አሸባሪዎችን የተቀላቀለ አንድ ሀበሻ ተገደለ
የኢትዮጵያው አገዛዝ በዜጎች ኮምፒዩተር ላይ የሚያደርገውን ስለላ የሚያጋልጥና የሚያከሽፍ ሶፍት ዌር በነፃ መቅረቡን የመብት ተሟጋቾች ይፋ አደረጉ
የአንድነት ፕሬዝዳንት “አቶ ግርማ ሰይፉ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን አስመልክቶ የተናገሩት የፓርቲው አቋም አለመሆኑን” ገለፁ
አንድነት የፀረ ሽብር አዋጁን ተቀብሎ እንደማያውቅ ገለፀ
ፓርቲው የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ የሚጠይቅ ዘመቻ ጀመረ
በሰሜን ጎንደር ህዝቡ ተሰብስቦ በአገዛዙ ታጣቂዎች ሰሞኑን የተገደሉት ሰላማዊ ሰዎች ጉዳይ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠየቀ
በኢትዮጵያ በርካታ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በጫት ሱስ መለከፋቸውንና ጉዳዩም አሳሳቢ መሆኑ ተገለፀ
የኔቫዳ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሁበር ጉዳይ በተያዘው ፍ/ቤት ሊታይ እንደሚቻል ገልፆ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ

No comments:

Post a Comment