Friday 14 November 2014

በድሬዳዋ ዩኒቪርሲቲ የሚማሩ የአፋር ተማሪዎችን ባህላዊ ወይም ሃይማኖታዊ ልብስ እንዳይለብሱ ተከለከሉ

አኩ ኢብን አፋር ለDaniel Tadese እንደዘገበው
ተማሪዎቹ እንደሚሉት ከሆነ በመመገቢያ ሬስቶራንትና ላይብረሪን ጨምሮ የባህል ልብስ ማለትም ሽሪጥና የመሳሰሉትን የባህል ልብስ መልበስ አትችሉም እንደሚባሉ በምሬት ገልፀዋል።
afar womenበኢትዮጵያ ህገ መንግስት የባህል፣የሃይማኖትና የብሄር እኩልነት አረጋግጠናል ይላል ግን ወያኔ የሚመራው የኢህአዴግ ፓርቲ በተግባር ላይ ማሳየት አልቻለም ይላሉ።
ከሁሉም በላይ ግን ይላሉ ተማሪዎች ያሳሰበን የሃይማኖት ጉዳይ ነው።
ሶላት ልንሰግድ የሚፈቅድልን ሃይማኖታችን በሚፈቅደው መልክ ሳይሆን ኢህአዴግ በሚፈልገው መልክ ነው።
ሶላት የምንሰግድበት ሰዓት ላይ ያስተምሩናል።
ሶላት እንደ ሃይማኖት አያዩትም አስፈቅደህ ሰግደህ ልትመለስ የማይታሰብ ነው።
ብንሰግድም በጀማኣ ወይም ተሰብስበን አብረን መስገድ አንችልም።
ስለዚህ አባቶቻችን በዲን (ሃይማኖት)ና በባህል መደራደር ሰላልስተማሩን ጉዳዩ በጣም አሳስቦናል ብሏል።
የአፋር ሙስሊም ተማሪዎች ቁጥር መጨመር ያልወደደው የወያኔ መንግስት በዩኒቨርስቲዎች ላይ ከፍተኛ እንግልት እያደረሰባቸው ይገኛል።
“ከዚህ በፊት ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ ብዙ የሙስሊም ተማሪዎች መባረራቸው የሚታወስ ሲሆን ከተባረሩት ውስጥ ብዙዎቹ የአፋር ተማሪዎች መሆናቸው ይታወቃል። በተለያዪ ዩኒቨርስቲዎች የአፋር ሙስሊም ተማሪዎችን ለማስፈራራትና ለማሸማቀቅ የተለያዩ ስልቶችን እየተጠቀሙ ይገኛሉ። ሰሞኑን በድሬ ዳዋ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የባህልና ሃይማኖታዊ ልብስ እንዳይለብሱ መከልከል መጀመሩ የዚሁ ሴራ አካል ነው ። በአሁኑ ሰዓት በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ 59 የአፋር ተማሪዎች እየተማሩ ይገኛሉ የሚሉ” የፖለቲካ ታዛቢዎች አሉ::

No comments:

Post a Comment