Wednesday 18 February 2015

OFC International Support Group Demands Abay Tsehaye Resign from Govt Position

The following Amharic statement is from the Oromo Federalist Congress (OFC) International Support Group. In the statement, the OFC International Support Group calls for the sacking of Abay Tsehaye from government position following the recently released audio of him threatening to rain down terror in Oromia unless the Addis Ababa Master Plan, which was categorically rejected by the Oromo people, was implemented by officials of the State of Oromia.
=============
ከኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ የአለም አቀፍ ድጋፍ ቡድን የተሰጠ መግለጫ
አባይ ፀሃዬ በአስቸኳይ ሥልጣኑን መልቀቅ አለበት!
ዛቻዉ በኦህደድ አመራሮች ብቻ ላይ ሣይሆን በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ነዉ።
የቀድሞ የፌዴራል ጉዳዮች ሚንስትር ሚንስቴር፣ የአሁኑ የጠቅላይ ሚንስተር አማካሪ አቶ አባይ ፀሀዬ በአዋሳ በተካሄደዉ የከተሞች ጉዳይ ስብሰባ ላይ “ማስተር ፕላኑ ይተገበራል! ማንም ቢቃወም ልክ እናስገባለን!” በማለት ዝተዋል።
ይህ ንግግራቸዉ የሥርዓቱ የሕዝብ ንቀት መገለጫ እንጅ የግለሰቡ ንግግር ብቻ አይደለም። አባይ ፀሃዬ በዚህ ንግግራቸው የሚከተሉትን ጥፋቶች ፈጽመዋል።
1. መንግስታዊ ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በሕዝብ ላይ የጦርነት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ አዉጀዋል። (መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከዚህ ቀደም በተፈፀሙትም የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ተጠያቂ ነዉ።)
2. የፌዴራሊዝም መርሆችን እና ሕገ-መንግስቱን በሚፃረር ሁኔታ የክልሎችን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት አፍርሰዋል። (የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 50-52)
3. ሕዝብን ያላሳተፈ ውሣኔ በማስተላለፋቸው የኢፌዴሪን ሕገ-መንግስት አንቀጽ 8 (የሕዝብ ሉዓላዊነትን)፣ የሕዝብ ተሣትፎ – አንቀጽ 42(2) እና (4) እንዲሁም 89(6) ንደዋል።
4. የሕዝብ ንቀት አሳይተዋል።
ሕዝብ እየናቁ፣ ሕግ እየጣሱ ሕዝብን ማስተዳደር ስለማይቻል በአስቸኳይ ከሥልጣናቸዉ ተነስተዉ እስካሁን ለፈጸሙት ወንጀሎች ተጠያቂ መሆን ይኖርባቸዋል።
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ የአለም አቀፍ ድጋፍ ቡድን
የካቲት 2015
—————
AbayTsehay201522

No comments:

Post a Comment