Sunday 22 February 2015

የ.ህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ለመከላከያ ምስክርነት ተጠርተው ባለመቅረባቸው በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ተባለ

imagesእሊና ቢሶቹ የ.ህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ለመከላከያ ምስክርነት ተጠርተው ሁለት ጊዜ በኢምቢተኝነት ሲቀሩ ለሶስተኛ ጊዜ በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ መቐለ የሚገኝ አንድ የወረዳ ፍርድቤት ዳኛ አዘዙ:: በከሳሽ  ብስራት አማረ በተከሳሽ  ኣስገደ ገ/ስላሴ የነበረ ክርክር መቋጫ ለማግኘት አቶ አስገደ ለመከላከያ ምስክርነት የጠራቸው አንጋፋ የህውሓት መሪዎች እነ  ሱዩም መስፍን፣ ኣርከበ ዕቁባይ፣  ስብሓት ነጋ፣  ኣባይ ፀሃየ ፣  ገብሩ ኣስራት ፣  ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ለ10/06/2007 ዓ/ም በመቐለ ሰሜን ወረዳ ፍርድ ቤት የ’ይቅረብ’ መጥርያ ትእዛዝ ተሰጧቸው ጀነራል  ፃድቃን ሲቀርቡ ሌሎች ግን በመቐለ ከተማ እያሉ ሳይቀርቡ በመቅረታቸው ለሁለተኛ ጊዜ የሰሜን ወረዳ ዳኛ በፖሊስ ተይዘው ለ13/06/2007 ዓ/ም ከጥዋቱ 3:00 ሰዓት እንዲቀርቡ ታዘው በድጋሚ በመቅረታቸው ዳኛው ለሦስተኛ ጊዜ  ለ24/06/2007 ዓ/ም ከጥዋቱ ሶስት ሰዓት ቀርበው የመከላከያ ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ለሶስተኛ ጊዜ ለሰሜን ወረዳ ፖሊስ አዛዞች ትእዛዝ ተሰጥተዋል። ይቀርባሉ ኣይቀርቡም እንከታተል። የዳኛው ድፍረት ቢገርመኝም በአረመኔ የህወሀት ባለስልጣኖች ሊደርስባቸው የሚችለውን ሳስበው በዳኛው ኩራት ተሰምቶኛል ። ለሆድ አደሮች የከፍተኛና ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች ከዚህ ትምህርት ለመቅሰምና ሀገራቹን ከአረመኔ መንግስት ነፃ ለማውጣት የበኩላቹን ትግል ይጠበቅባቹሃል። 

No comments:

Post a Comment