Wednesday 14 January 2015

ከልለው ኡርጋ:- የወያኔ ታላቅ ሴራ በሕዝብ ኃይል ይከሽፋል!

ወያኔ ላለፉት 23 ዓምታት ከከተማ አስከ ገጠር፣ ኦሮምያን ተቆጣጥሮ እና ተጭኖ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ያደረሰው እና እያደረሰ ያለው መጠነ ስፊ ግፍ ከማናችንም አምሮ የሚጠፋ አይደለም። በዘመናዊ መሳርያ እና ዘመናዊ መሳሪያ በታጠቁ ሰራዊት እና ለሆዳቸዉ ባደሩ ህሊና-ቢስ የደህንነት ኃይሎች ታግዞ ብዙዎችን ገድሎል፣ አስሮል፣ ከቀያቸው አፈናቅሎል፣ ብዙዎችን ደግሞ ለስደት ዳርጓል።
በማን አለብኝነት የኦሮሞ ተቋማትን፣ ድርጅቶችን እና ማህበራትን ዘግቶል። አባላቱን እና ደጋፊዎችን ከኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር ጋር ግንኙነት አላቹህ በማለት፣ በሐሰት ከሶል፣ አስሮል፣ በዛቻ አና ማስፈራራት ትውልድ ስፈራችዎን ለቀው እንዲሰደዱ አና የአውሪ እና የባህር እራት እንዲሆኑ አድርጎል፤ ሀብት ንብረታቸውን ወርሶል፣ ዘርፎል የተቀሩትን በደህነት አሮንቆ እንዲዘፈቁ አድርጓል። ይህን ሁሉ በደል እና የከፋ ጭቆና በሕዝባችን ላይ አድርሶል አሁን ግን ይህ ሁሉ ታሪክ ሆኖ የሚቀር የሆናል – በጭቁን የኦሮሞ ልጆች።
ወያኔ ከሌላው ሕዝብ በተለየ የኦሮሞን ሕዝብ ኢላማ ያደረገው ወይም ያነጣጠረው አያሌ ምክንያቶች ውስጥ በተፈጥሮ ሀብቷ፣ በአልበገር ባይነቱ፣ ባህል እና ታሪኩን ጠባቂነቱ የቆዳ እና የሕዝብ ብዛቱ ለአብነት ያህል የሚጠቀሱ ናቸወ። ለነገሩ ያለፉትም የኢትዬጵያ ገዥዎች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ተመሳሳይ ጭካኔ የተሞላበት ግፍ እና መከራ አድርሰዋል። አንዳቸዎም ግን ስልጣን በቃን በሕዝብ ላይ ግፍ መስራት አንገሽገሽን ብለው ዙፋናቸውን የለቀቁበት ግዜ እና ዘመን በዚያች ሀገር ታሪክ ዉስጥ የለም። መከራ ቀማሹ የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች የተጨቆኑ ሕዝቦች ጋር በመሆን ሰባዊ አና ዲሞክራሲያዊ መብቱን ለማስጠበቅ ታግሎል እየታገለም ነው ለዚህም ይህ የማይባል መጠነ ሰፊ መሰዋትነት ከፍሎል እየከፈለም ይገኛል።
ብዙዎች ለዛሪዋ ቀን ለመድረስ ውድ ሕይወታቸውን መስዋትነት ከፍለዋል እየከፈሉም ነው። እስከ አሁን የኦሮሞ ሕዝብ የተቀዳጀው ድል የብዙ የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የሕይወት መስዋትነት ውጤት ነው። ባሳለፍነው በሚያዝያ እና የግንቦት ወር የኦሮሞ ተማሪዎች የከፈሉት መስዋትነት ከሕፃን እስከ አዋቂ የተካፈሉበት እና አልበገር ባይነታቸዎን ያሳዩበት ከታንክ እና መትረየስ ጋር ከታጠቀ አረመኔ የወያኔ መንግስት ጋር የተጋፈጡበት እና ለመብታቸው ሲታገሉ የተሰውትን የኦሮሞ ሕዝብ ምን ግዜም አይረሳቸውም። ኦሮምይም ለመብታቸው ሲሉ ሲታገሉ የተሰውትን ስትዘክር ትኖራለች። ወያኔም ከሶ በፊት እንደነበሩ አምባገነን ገዥዎች በሕዝብ ኃይል ትገለበጣለች። ሕዝብ ያልመረጣቸዉ ለሕዝባችው አደገኛ ናቸው እና። በዚያች ሀገር ታሪክ ውስጥ በሕዝብ የተመረጠ እና ስልጣን የይዘ ገዢ የለም። በ1997 ዓም ምርጫ ብናስታዎስ ወያኔ በሕዝብ አልተመረጠም 1928 ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሆኑ ደርግ ሕዝብ ፈልጓቸው ሳይሆን በጉልበት ነው ሥልጣን የያዙት ይህ የሚያሳየው ሁሉም አምባገነን መሆናቸው እና በሕዝብ ኃይል እየተዋረዱ ከስልጣ መዉረዳቸዉ እና ማለፋቸውን ነው።
ችግሩ አንዱ አምባገነን ከሌላው ትምህርት አለመውሰዱ ነው። አምባገነን በአምባገነን መተካካቱ ነው። በዚህም ምክንያት የዲሞክራሲ እና ሰባዊ መብቶች በኃይል እየተነጠቁ በየቀኑ ብዙ ሰው አልቆል አያለቀም ነው ምሁሩን ፣ ወጣቱን፣ ሕፃናትን፣ ሴት እና ወንድ ሳይሉ የንፁሀን ሕይወት አጥፍትተዋል። የካቲት 1966ዓ.ም. አብዬት ከ40 ዓመት በላይ የቆይው የዘውድ ስርዕት የገረሰሰው የሕዝብ ብሶት ውጤት ነው፤ ይሁን እንጂ ሕዝብ ሲመኘው የነበረው ዲሞክራሲ አውን ሳይሆን ቀረ አና በሌላ አምባገነን ተተካ። 1983 ብንመለከት በሕዝቦች ትግል የመጣ ውጤት አንጂ አምባገነኖቹ እንደሚሉት የአንድ ብሔር የትግል ውጤት አይደለም በሽዎች የሚቆጠሩ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መሰዋትነትን ከፍለውበታል። አሁንም አምባገነኑ የወያኔ መንግስትን ሕዝብ ሰቆቃው በቃን አንገሽገሸን ሳንፈልጋቸው 23 ዓመታቸው እያለ ነው እና ከወዲሁ የአምባገነን አገዛዝ ማክተሚያ እንደሚሆን አመላካች ነገሮች አየታዩ ነው። በሚያዝያ እና ግንቦት ወር 2014 ብቻ በመላዉ ኦሮምያ የተደረገው የኦሮሞ ተማሪዎች የተቀናዠ እንቅስቃሴ የመጭዉ ብሩህ ተስፋ የኦሮምያ አዲሱ ትውልድ አልበገር ባዩ ነው እንደሆነ የሚያረጋግጥልን እውነት ነው።
ድል ለኦሮሞ ሕዝብ!

No comments:

Post a Comment