Tuesday 1 April 2014

ኢትዮጵያ ውስጥ የኦሮሞ መብት ተከብሮ አያውቅም::


የኦሮሞ ህዝብ ሰራተኛ ነው::  የኦሮሞ ህዝብ የተማረ ነው :: የኦሮሞ ህዝብ ሰው አክባሪ ነው::  የኦሮሞ ህዝብ አገሩን ለማሳደግ የሚደክም ህዝብ ነው::  የኦሮሞ ህዝብ በወደደና ባመነ፣ በተማረና ባስተማረ፣ ስራ በሰራና አገር ባሳደገ – ይህ ሁሉ በደልና ግፍ ለምን?! 

1,ህዝባችንን አትበድሉ አትጨቁኑ ብሎ መተየቅ...አሸባሪ ነክ ( ኦነግ)  ነህ ተብሎ ያሳስራል::

2,  ተማሪዎቻችንን ከትምህርት ገበታቸው ላይ አታባሩ ብሎ መጠየቅ ….አሸባሪ ነክ ( ኦነግ)  ነህ ተብሎ ያሳስራል::

3,መምህሮቻችንን በነጻነት እንዲያስተምሩን ይሁን ብሎ መጠየቅ ….አሸባሪ ነክ ( ኦነግ)  ነህ ተብሎ ያሳስራል::

4,ገበሬዎቻችንን ከመሬታቸው አታፈናቅሉ ብሎ መጠየቅ ….አሸባሪ ነክ ( ኦነግ)  ነህ ተብሎ ያሳስራል::

5,ሰራተኞች እና አርቲስቶች ከኦነግ ጋር ግኑኙነት አላችሁ ተብለው ለስራ እንደወጡ አልያም ከቤታቸው ታፍነው የተገደሉ እና የታሰሩ መጠየቅ … አንተ...አሸባሪ ነክ ( ኦነግ)  ነህ ተብሎ ያሳስራል::

6, አላወቁም እንጂ ሁሉም የኦሮሞ ህዝብ ነጻነቱን ፈላጊ ነው::

7,የኦሮሞን ነጻነት የምናፍቅ በነጻነት መኖርን የምመኝ ስለ ነጻነት የምታገል ምርጥ የኦሮሞ ልጅ ነኝ::

8,ገበሬው ከመሬቱ ሲፈናቀል የሚያመኝ መብቱ ሲነካ   የማልወድ  ምርጥ የኦሮሞ ልጅ ነኝ::

9,ተማሪው ተምሮ ወገኑን ይረዳል አገር ይረከባል ሲባል በጭቆናና በበደል በግፍ ከትምህርት ገበታው ሲባረር የሚያመኝ ምርጥ የኦሮሞ ልጅ ነኝ::

10, አስተማሪው የነገ አገር ተረካቢ ለማፍራት ሲጥር ሲደክም በኦሮሞነቱ ብቻ ከመምህርነቱ ሲነሳ ሲባረር  የሚያመኝ ምርጥ የኦሮሞ ልጅ ነኝ::

11, ሰራተኛው ኦሮሞ ስለሆነ ብቻ ለኦሮሞ ነጻነት ግንባር ትረዳለህ ተብሎ ከስራው ቦታ ታፍኖ ተወሰዶ ሲገደል፣ ሲታሰርና ሲባረር፤  የሚያመኝ ምርጥ የኦሮሞ ልጅ ነኝ::

12,! አርቲስቱ ሲያቀነቅን፣ ሲያዜም ይሄ ለቅስቀሳ ነው፣ ፖለቲካዊ አጀንዳ አለው ተብሎ ሲታሰሩ ሲገረፉ ሳይ  የሚያመኝ ምርጥ የኦሮሞ ልጅ ነኝ::

13,ኦሮሞን ነጻነት ለማውጣት የምታገል የምደክም የምሞት ስለኦሮሞ ህዝብ የምቆረቆር...ምርጥ የኦሮሞ ልጅ ነኝ::

No comments:

Post a Comment