አኩ ኢብን ከአፋር
በአፋርኛ
Cube waak suge ayro tewqeemih
Macal oggola anu amo ramna
cube wayni hagga yoo heekkal
anu luk suge ayro
luk raaqe.
cube wayni hagge yoo heemih
woh amo ramma yol
makko.
Cube waak suge ayro tewqeemih
Macal oggola anu amo ramna
cube wayni hagga yoo heekkal
anu luk suge ayro
luk raaqe.
cube wayni hagge yoo heemih
woh amo ramma yol
makko.
ይሄ ዘፈን በአማርኛ ሲተሮገም
«ያላሰብኳትን ፀሃይ ብትወጣልኝም
እኔ በነበርኩበት አለሁኝ፣
ቢሆንም ይሄ ግን አንገቴን እንድደፋ አላደረገኝም!» ይላል።
እኔ በነበርኩበት አለሁኝ፣
ቢሆንም ይሄ ግን አንገቴን እንድደፋ አላደረገኝም!» ይላል።
የአፋር ህዝብ በእርግጥ ያልጠበቀውን ፀሃይ ቢወጣለትም ችግሩ ግን የባሰ ሆኗል። የአፋር ህዝብ በመብቱ ፣ በሀገሩና በሃይማኖቱ በምንም አይነት መንገድ የማይደራደር በራሱ የሚተማመን ታላቅ ህዝብ ቢሆንም የወያኔ ስርዓት የአፋር ህዝብ ከፓለቲካ ጋር ያለውን ግንኙነት እንደ ደካማ ጎን በመጠቀም የአፋር ህዝብን በተዘዋዋሪ በቀኝ ግዛት እየገዛ ይገኛል። ለ23 አመታት የምንሰማው ወይም የምናየው ኢህአዴግ የብሄር ብሄረሰቦች መብትን አስከበሯል ሲባል ነው። ስለዚህም የአፋር ህዝብ ይህ የበሄር በህረሰቦች መብት ካገኙ ህዝቦች አንዱ ነውም ይሉናል። በነገራችን ላይ የብሄር ብሄረሰቦች መብት ማለት ባህላዊ ጭፈራ በመጨፈር የሚመዘን አይደለም።
ይሁንና እኔ በግሌ የፈደራሊዝም ስርዓት ከሚፈለጉ አንዱ ነኝ። ግን አሁን ያለው የወያኔ የውሸት ፈደራሊዝም ሳይሆን በክልሌ ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት ራስን በራስ መምራት ስችል፣ በቋንቋዬ መማር፣ ማስተማርና መስራት ስችል እንዲሁም በክልሌ ያለማንም ጣልቃ ገበነት የፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲ ማርቀቅ ስችል። በእነ ደብረፅዮን ሪሞት ኮንትሮል ሳልሆን ራሴ በመረጥኩት መሪ መተዳደር ስችል፣ መሪዎቼን መምረጥ ብቻ ሳይሆን አስተዳደሩን በመረጥኩበትን ቃል ጠብቆ ካላገኘሁ በነፃነት መቃውም እና ሃሳቤን በነፃነት መግልፅ ስችል፣ ወዘተ…. ያኔ መብቴ እንደተከበረልኝ እመሰክራለሁ። ግን «የአፋር ህዝብ ስለፖለቲካ አያውቅም» ብሎ በህወሃት ሪሞት ኮንትሮል በሚሰሩ ቀፎዎች «ልምራህ» ሲባል አልመራም ማለት መብቱ ነው።

በባለፉት 23 አመታት የአፋር ህዝብ እንደ ማንኛውም ዜጋ የኤሌክትረክ ብርሃን መግኘት አልቻለም። ይህን ጥያቄ አንድ የአፋር ህዝብ ተወካይ የሆኑት በፓርላማ አባል በ2002ዓ.ም አቶ መለስ በጠገኙበት አይናቸው ጭፍን አድርገው «የአፋር ህዝብ ዘላለም በጨላማ እንዲኖር የተፈረደበት ምክንያት ምንድነው?» ብለው ጠይቀው አቶ መለስ ዜናዊ ደግሞ ዘና ብለው «አዎ የአፋር ህዝብ የኤሌክትሪክ ችግር እንዳለበት እናውቃለን ግን ለኤሌክትሪክ ማመንጫ እየተገነቡ የሚገኙ ግድቦች ሲጠናቀቁ ይስተካከላል» ብለው ረዘም ያለ ቀጠሮ ሰጥተዋል። ቢሆንም ዛሬም ከጨለማ አልወጣንም መንግስት የሚባል ነገር በአፋር ክልል የለም። የአፋር ህዝብ ብሶቱን «አቤት» የሚልበት ሚዲያ የለውም። በዳሉል ወረዳ የሚገኙ 12 ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ መብራት የሚባል ነገር የላቸውም። ለወደፊት ተስፋ እንኳን የሚሆን የተጀመረ ስራም የለም!
ነዋሪዎች ለሚመለከተው አካል ሲጠይቁ አነሱ ደግሞ «መንገድ የለም» ይላሉ። በተለይ አንዳንድ በጐ አድራጊዎች የሆኑ የውጭ ድርጅቶች ለዳሉል ህዝብ የሚጠጣ ውኃ ለማውጣት ቢሞክሩም ማሽኑ የሚገባበት መንገድ አጥተው ይመለሳሉ። ታዲያ መንገድ መስራት ያለበት ማን ነው ? ለመሆኑ ለአፋር ክልላዊ መንግስት የሚሰጠው አመታዊ በቢሊዮኖች ብር የሚቆጠር ገንዘብ የት ነው የሚገባው? በተቀሩት 31 ወረዳዎችም ተመሳሳይ ሆኔታ ነው ያለው። እነዚህ በኢህአዴግ «የከፋፍለህ ግዛ» ህዝብን በጎሳና በዘር ለመከፋፈል የሚያባክኑት ገንዘብ የህዝብ አይደለም እንዴ? የሄ የአብዴፓ አመታዊ በዓል ሲከበር የሚያጠፉት በሚሊዮን ብሮች የሚቆጠረው ገንዘብ የህዝብ አይደለም እንዴ?
የተከበራችሁ የአፋር ህዝቦች ሆይ ይሄን ሁሉ መብቶቻችንን ለማስከበር መነሳት ያለብን አሁን ነው!!.
No comments:
Post a Comment