Thursday, 19 June 2014

ነውረኛዋና ሰላይዋ ዝማም (ኢየሩሳሌም አርአያ)

ዝማም ትባላለች፤ የሕወሐት ታጋይ ናት። ባለቤቷ አቶ ቢተው በላይ ይባላሉ። ቢተው እስከ1993 ዓ.ም የደቡብን ክልል በበላይነት ሲያሽከረክሩና ሲመሩ የቆዩ ናቸው። በመጋቢት 93 ከአቶ መለስ ጋር በተፈጠረ የፖለቲካ ውዝግብ ከሌሎች ጋር ተነጥለው ወጡ። ከዚያም ከደቡብ ክልል ፕ/ት አባተ ኪሾ ጋር በሙስና ተከሰው ዘብጥያ ወረዱ። ፍ/ቤት መቅረብ እንደጀመሩ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ጋር ለዜና ዘገባ ስንመላለስ የቢተውን ባለቤት ዝማምን ተዋወቅኳት። በክልል 14 ቢሮ ተመድባ ነበር የምትሰራው። ባለቤትዋ ከታሰረ በኋላ ግን ዝቅ ተደርጋ በቀበሌ ደረጃ ተመደበች። ዝማም በርካታ ምስጢሮችን ታውቃለች። አርከበ ወደ ከንቲባነት ሊመጡ እንደሆነና ሌሎች ቁልፍ መረጃዎችን አቀብላኝ በኢትኦጵ ጋዜጣ ሰርቼዋለሁ።
..ዝማምን ዛሬ እስር ቤት የሚገኘው የደህንነት ሹም ወ/ስላሴና አየር መንገድ ያለው ሃይሌ አጠመዷት። የሕወሐት ነወረኛ ደህንነቶች ጋር መጠጥ እየተጋተች አንሶላ እንደተጋፈፈች ስገልጽ ከልብ እያዘንኩና ይህን ዘገባ ለምታነበው ሴት ልጇ እየተሸማቀቅኩ ነው። ነገር ግን ይህን ነውረኛ ድርጊቷን ባልዋ አቶ ቢተው እስር ቤት ሆኖ ያውቅ ነበር። እቤቱ ውስጥ በፓርቲው አንጃዎች ይካሄድ የነበረ ስብሰባ እየተቀረጸ አቶ መለስ ዘንድ ተልኳል። ይህ ሁሉ በዝማም የተከናወነ ነበር።… ሳይታወቅ የቆየውን “ኢየሩሳሌም አ..” የብእር ስም በመጠቆምና ለነወ/ስላሴ አሳልፋ በመስጠት የግድያ ሙከራ እንዲፈጸምብኝ ያደረገችው ዝማም ናት።
ንጉሴ የተባለ መቶ/አለቃ ተገድሎ ሬሳው ጅብ እንዲበላው የተደረገው በዝማም የሴራ ተባባሪነት ነው። (ታሪኩ ረጅም ሲሆን ይህን ጠንቅቀው የሚያውቁት መጽሃፍ ጽፈው ሲያበቁ ይህን ታሪክ አለማካተታቸው ያሳዝናል) ..እንደ ዝማም ሁሉ ባለቤትዋ ከ6 አመት እስር በኋላ ሲፈታ ያሳየው መገለባበጥ አሳፋሪ ነበር። ከአቶ መለስ ተጠግቶ የአፋር ክልል ባለስልጣን ሆነ። ከዚያም ወደ መከላከያ ኢንጂነሪንግ አመራ።ጭራሽ በዚህ ዓመት በሕወሐት የተፈጠረው ቀውስ “አስታራቂ” ሽማግሌ ሆኖ ተሰየመ። የስብሃት ተከታይነቱንም አረጋገጠ። ባልና ሚስት እጅግ የለየለት ርካሽ ቁማር የተጫወቱ ናቸው። …ባለፈው ሳምንት አንድ ወጣት ልጃቸው በሞት መለየቱን ሰማሁ። ከነርሱ ተግባር ጋር ልጁ የሚያገናኘው ነገር ስለሌለ በመሞቱ ከልብ አዝኛለሁ። ፈጣሪ ነፍስ ይማር!!

No comments:

Post a Comment