Wednesday, 26 November 2014

የሚሊዮኖች ድምፅ ቀጣይ መርሀ ግብሮች

በዚህ ዘመን ያለው የግፍ አገዛዝ የማይነካው የህብረተሰብ ክፍል እንደሌለ፤ በየእስር ቤቱ ታጉረው የሚገኙት የህሊና እስረኞች ዓይነትና ብዛት ማየቱ ብቻ በቂ ነው። በበርካታ ሺዎች የሚቆጠሩ የህሊና እስረኞች በዛሬዋ ኢትዮጵያ በእየስርቤቱ እየተሰቃዩ ነው የሚገኙት። በመሆኑም እስርና እንግልት በሀገራችን ያበቃ ዘንድ ድምፃችን ከፍ አድርገን ማሰማት ይኖርብናል። በዛሬው ዕለት የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች በዋናነት እነ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ እና ሌሎች በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የህሊና እስረኞች ታስበው የሚውሉ ሲሆን፤ ሰሙኑ እንደነበረው ሁሉ ዛሬና በሚቀጥሉት ቀናት በሚኖሩት መርሀ ግብሮች ላይም ህብረተሰቡ በሶሻል ሚዲያው ላይ ድምፅ እንዲያሰማ በአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
እንደዚሁም፤ ለተለያዩ ተቋማት በኢሜልና በልዩ ልዩ መንገድ በኢትዮጵያ ስላለው የእስረኞች አያያዝና ሁኔታ መልዕክት በማስተላለፍ የዜግነትና የሀገር ግዴታችሁን የተወጣችሁ ሁሉ ምስግናችን ይድረሳችሁ፤ አሁንም ቢሆን ከሶሻል ሚዲያው ባለፈ መልኩ ጠንካራ ተፅዕኖ ለመፍጠር ዘመቻውን ሰፋ አድርገን ለማካሄድ ጥረት እያደረግን ነው ያለነው፤ ተሳተፉ፤ ድምፃችሁን አሰሙ። በቀጣይ ቀናት የሚኖሩት መርሀ ግብሮች፦
ነገ ሀሙስ፦ እነ ተመስገን ደሳለኝና ሌሎች ጋዜጠኞች
ዓርብ፦ የሞስሊም መፍትሄ አፈላለጊ ኮሚቴ አባላት
ቅዳሜ፦ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንእሁድ፦ እነ አንዷለም አራጌና ሌሎች የፖለቲካ ታሳሪዎች
እንደዚሁም እሁድ ዕለት በአንድነት ጽ/ቤት ደማቅ የመዝጊያ ስነስርዓት ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ይኖራል። በዕለቱ ሁሉም ሰው ጥቁር ልብስ ለብሶ እንዲመጣ የአንድነት ወጣቶች ከአሁኑ እየቀሰቀሱ ነው የሚገኙት። ከዚህም በተጨማሪ ባለፈው በታላቁ ሩጫ ምክንያት የተላለፈው ጋዜጠኛ ሃይለመስቀል ሽዋምየለህ የሚያቀርበው ጋዜጠኝነትና የእስር ፖለቲካ የሚለው ፅሁፍ በመዝጊያ ስነስርዓት ላይ ያቀርባል፤ በመዝጊያው ስነስርዓት ላይ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ታዋቂ እንግዶች ይገኛሉ ተብሉ ይጠበቃል።
ክብር ለህሊና እስረኞች!
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ10801574_734033110014959_5988330264336186554_n

No comments:

Post a Comment