በጃል/Jaal ጀዋር መሐመድ*
ሰሞኑን አንድ የOMN ጋዜጠኞች ከአብዱላ ገመዳ ጋር ቁጭ ብለው የሚያሳይ ፎቶ በኢንተርኔት ከተሰራጨ በኋላ ትንሽ ቀዝቀዝ ብሎ የነበረው የግልገል-ነፍጠኞች በሽታ ማለትም ኦሮሞ-ፎቢያ (Oromo-phobia) እያገረሸባቸው ይመስላል። ጋዜጠኞቹ፣ በምን ሁኔታ ከባለስልጣኑ ጋር እንደተጋናኙ በስፋት ገልጸዋል። ስብሰባውን እና የሚጠበቀውን የተቃውሞ ሰልፍ ለመዘገብ ወደ ስፍራው ተጓዙ። ሲደርሱ፣ ፖሊሶች እነሱንና ሌላውንም ህዝብ አባረሩ። ካሜራ ይዘው መግባት አለመቻላቸውን ሲያውቁ እቃቸውን ትተው ተመሳስለው ገቡ። በዚያ መልኩ መግባት የቻሉት እነሱ ብቻ ሳይሆኑ፣ ሌሎች ጋዜጠኞችን ጨምሮ 39 ኦሮሞዎች ባብዛኛው ለተቃውሞ የሄዱ ነበሩ።ስብሰባው ላይ ጋዜጠኞቹ ጠንካራ ጥያቄዎችን አቀረቡ። በተቻላችው አቅምም፣ በስልክ መቅዳት ቻሉ። ስብሰባው ሲያልቅ፣ በግል ልናነጋግራችሁ፣ እንፈልጋለን ተባሉ። ከነዚህ ባለስልጣኖች ጋር ቃለ-መጠይቅ ለማድረግ፣ ለቀናት ጥያቄ ሲያቀርቡ ነበር። እናም በግል እናናግራችሁ ሲባሉ፣ ያ ሙከራቸው የተሳካ መሰላቸው እና ተከትለው ወደ ቀጣዩ ክፍል ገቡ። ነገር ግን እንዳሰቡት አልሆን። ክፍሉ ለእራት የተዘጋጀ ነበር። ቃለ-መጥይቁን እንደማይፈቅዱ እና አብረው ቁጭ ብልው የሚለዋወጡትን ንግግር እንኳን፣ መቅዳት እንደማይችሉ ተነገራቸው። ከ20 ዳቂቃ የማግባባት ሙከራ በኋላ፣ ጥለው ወጡ። ፎቶው የተነሳው፣ ይህን የማግባባባት ጉትጎታ ሲያደርጉ ነው። በቃ፣ ይህ ነው ታሪኩ።
ታዲያ የሚገርመው የግልገል-ነፍጠኞቹ ጩሀት የባሰበት፣ ጋዜጠኖቹ በዚህ መልኩ ዝርዝር ዘገባ ካቀረቡ በሃላ መሆኑ ነው። ለመሆኑ እንዚህ ግልግል-ነፍጠኞች የሚቆጣጠሩት ሚዲያ (media) አባ-ዱላን ወይንም ሌላ ባለስልጣን ጋር ለ exclusive ቃለ-መጠይቅ ቢጋበዙ፣ እምቢ ይላሉን? እንተዋወቃለን እኮ! OMN አይደለም ከኦሮሞ ብሄር የፈለቀን ሰው ይቅር እና ‘ኦሮሞ’ የሚለውን ቃል የሚጠየፉ፣ ማንነታችንን የሚያንቋሽሹ፣ የፖሊቲካ አመለካከታቸው እንደ አረጀ ፈረሰ የተንሸዋረረ የneo-neftegna መሪዎችን እንኳን፣ የጋዜጠኝነት ሙያ በሚጠይቀው መሰረት፣ በክብር ለማስተናገድ የተቋቋመ ድርጅት ነው። ይህንን መርህ ደግሞ ባለፉት 10 ወራት በተግባር አሳይቷል። የሰማያዊ ፓርቲን የተቃውሞ ሰልፍ ቢጤ ግርግር፤ በ’አንድነት’ ቡድን ላይ ወያኔ የወሰደውን የማፍረስ ሴራ፤ የግንቦት-ሰባትን የኤርትራ ድንፋታ – በሚጋባ ሳያሳንሱ ሳያጋንኑ ዘግበዋል። ጋዜጠኝነት ማለት፣ የበሬ ወለደ breaking news እያራገቡ፣ እንደ አህያ ማናፋት አይደለም። ጋዜጠኝነት፣ ህዝቡ ማወቅ ያለበትን ነገር፤ የት፣ እንዴት፣ መቼ፣ በማን እንደተፈጸመ መርምሮ verifiable fact ማቅረብ ነው። OMN – በህዝብ መዋጮ የሚተዳደር የህዝብ (public) ሚዲያ (media) ነው። የኦሮሞን ህዝብ እውነት (truth) በእውነተኛ መንገድ ለማቅረብ ነው የተቋቋመው። ይህ ማለት ግን፣ የሌላውን ህዝብም ሆነ ቡድን እውነታ (ቡድኑ የኦሮሞ ህዝብ ጠላትም እንኳ ቢሆን) የማፈን ፍላጎት የለውም።
በነገራችን ላይ፣ ዛሬ የኦሮሞ ጋዜጠኖች ከአንድ የኦሮሞ ባለስልጣን ጋር ፎቶ ላይ ታዩ ብለው፣ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉት ሰዎች፣ የራሳቸውን ገመና መፈተሽ አለባቸው። የብአዴኖቹ እነአዲሱ ለገሠ፣ ህላዊ ዮሰፍ፣ ጀነራል አበባው፣ ታደሠ ከዛም አልፎ፣ የወያኔ ቱባዎች እነስበሃት ነጋ፣ ጻድቃን ገብረ-ትንሳይ፣ አባይ ጸሃየ፣ ሳሞራ ዩኑስ – እዚህ ሀገር (U.S.A.) ሲመጡ የአሜሪካን ምርጥ steak ከBlue Label ጋር፣ የሚጋበዙት ከድሮ የክፍል ጓደኞቻቸው ከአሁኖቹ ነፍጥ-አልባ የDC አርበኖች ጋር፣ መሆኑን በተጨባጭ እናቃለን። ግማሹን፣ በአይኔ በብሌኗ አይቻለሁ። የዛሬን አይበልው እና፣ አንድ ሰሞን፣ ቤተኛ እስከመሆን ደርሰን እንደነበር አትርሱ።
ታዲያ ዛሬ፣ የኦሮሞ ጋዜጠኖች (ልብ በሉ የፖሊቲካ መሪዎች አይደሉም) ሙያዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ከአባዱላ ጋር ቢገናኙ፣ ይህን ሁሉ ጩሀት ምን ቀሰቀሰው? መልሱ ቀላለ ነው። ለግልገል-ነፍጠኞች እና ወያኔዎች ከምንም እና ማንም በላይ የሚያስፈራ ነገር ቢኖር፣ እርስ በርሳቸው ጠላቶች ናቸው ብለው የሚጠብቋቸው ኦሮሞዎች አብረው መታየት ነው። እንደነሱ ፍላጎት፣ ኦሮሞ በቡድን ተከፋፍሎ ሁሌም አንዱ አንዱን እያብተለተለ፣ አንዱ የኦሮሞ ቡድን ከነሱ ጋር አብሮ ሌላ ቡድን ውስጥ ያሉ እህቶች እና ወንድሞቹን እየዘረጠጠ፣ እራሱንም እያዋረደ፣ ባዕዳንን እያስፈነደቀ፣ ቅሌት ሲሸከም ነው። እነሱ ማየት የሚፈልጉት እና የለመዱት የኦሮሞ ልጆች በመኢሶን፣ በኢጭአት፣ በኦነግ፣ በኦህዴድ፣ በኦዲፍ፣ በኦፍሲ … የዳዉድ-ኢብሳ-ኦነግ፣ የከማል-ገልቹ-ኦነግ፣ የገላሳ-ዲልቦ-ኦነግ እንዲሁም የሌንጮ-ለታ-ቡድን ፣ የመረራ-ጉዲና፣ የቡልቻ-ደምቅሳ ተብሎ፣ ተደርድሮ እየተኳረፈ፤ ከቻለም እየተታኮሰ፣ ሲፋጭ ማየት ነው። እንደነሱ ፍላጎት፣ አባዱላ አብዲ ፊጤን በታንክ ደምስሶ ሲሸልል፣ ወይንም አብዲ ፊጤ አባዱላን በአስቀያሚ ስድብ ዘርጥጦት ሲያዋርደው፣ አይተው ሁለቱንም ለmutual self-destruction ማበረታታት ነው። እስቲ ልብ በሉ። VOA እና የጀርመን ራዲዮ አማርኛ ፕሮግራሞች የኦሮሞ ድርጅቶች ሲከፋፈሉ፣ ተፎካካሪ መሪዎችን ጋብዘው ሲያነታርኩ እንጂ ተመልሰው ህብረት ሲመሰርቱ ዘግበው ሰምታችሁ ታውቃላችሁ?
ግልገል-ነፍጠኞች እና ወያኔዎች የኦሮሞን መከፋፈል፣ መነታረክ የሚፈልጉትም ያለ ምክንያት አይደለም። የተከፋፈለ እና እርስ-በርሱ የሚናከስ ኦሮሞ፣ እራሱን በራሱ እያዳከመ ለጠላቶቹ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል። እንደዚያ የተከፋፈለ ኦሮሞ ሲኖር፤ ባለጋራዎቹ በፖሊቲካ ጉዳዮች ላይ በጅምላ ከመደራደር ይልቅ፣ በችርቻሮ አንዱን ወይም ሌላውን ቡድን ለማባበል እና ብሎም ለመግዛት ያመቻቸዋል። አንዱን ቡድን አቅርበው፣ ሌላውን በጠላትነት ፈርጀው፣ አያባሉ፣ እሾህን በሾህ ያወጡታል። ለረጅም ዘመናትም ሲሆነ የቆየውም ይሄው ነው። ያአለም ያደነቀው የኦሮሞ ራባ ዶሪ ጦር፣ በአቢሲኒያን ህይሎች ተሸንፎ፣ ሃገሩ በባዕዳን ቅኝ አገዛዝ ስር የወደቀችው ዋናው ምክንያት፣ ይህ ክፍፍል ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በነታደሰ ብሩ፣ በነኤሌሞ ቂልጡ፣ በነዋቁ ጉቱ እና ሌሎች መስራችች የተጀመረው የኦሮሞ ብሔራዊ አንድነት ግንባታ ከአበባ ወደ ፍሬ፣ ተሸጋግሮ የችርቻሮ ፖሊቲካን ምህዳር እያጠበበ ያለ አስደማሚ የኦሮሞ ብሄረተኘት፣ እውን ወደመሆን እየተጠጋ ነው። ይህ እውነታ ነው፣ ግልገል-ነፍጠኞችን እና ወያኔዎችን እንቅልፍ ነስቶ፣ የሚያቁነጠንጣቸው። አብደው ጨርቃቸው ጥለው ይሄዷታል እንጂ፣ የኦሮሞ ልጆች አንድነታቸውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጠናከሩ ወደ ነፃነት የሚያድርጉት ጉዞ ለሰከንድም፣ አይገቱትም።
No comments:
Post a Comment