ከከልለው ኡርጋ | Gurraandhala 9, 2015
በ 21 ክፍለ ዘመን አደጉ እና ሰለጠኑ የምንላቸው የዓለማችን ሀገሮች የእንሰሳት መብት ከሰው ልጅ መብትባልተናነሰ ሁኔታ የሚከበርበት ደረጃ ላይ ተደርሶል። የነሱን መብት መጠበቅም ልክ እንደ አንድ የእድገት ደረጃ መቆጠር ከጀመረ ውሎ አድሮል። ለዚህም ይመስላል መሀተመ ጋንዲ በአንድ ወቅት ¨የአንድ ሕዝብ ታላቅነት የሚዳኝው ለእንሰሳት በሚሰጡት እንክብካቤ ነው ያሉት¨።
ዛሬ ግን ምስኪኑን ለፍቶ አደር የኦሮሞ ገበሬ ለነፃነት፣እኩልነት፣ ለሕግ የበለይነት ፣ለዲሞክራሲ እና ፍትህ ብሎ የሚታገለውን እና ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት አልገዛም ያለውን ሰባዊ ከሆነ የፍጡር ደረጃ አወረዱት። ዛሬ ዓለም ለእንሰሳት ከምትሰጠው ክብር በታች አደረጉት ልክ እንዳልባሌ ነገርቆጠሩት። ያቺ ሀገር ሕፃናት የሚገደሉበት፤ ነፍሰ ጡር እና አዛዉንቶች የሚደበደቡበት ሰውን የሚያክል ክቡር ፍጡርን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉ በኃላ መሬት ለመሬት እየጎተቱ በአደባባይ መስቀላቸው ያቺ ሀገር መንግስት አልባ የተደራጁ የሽፍቶች ቡድን የምትገዛ መሆኖን ማሳያነው።
እንደዚህ ዓይነት ጭካኔ የተሞላበት ኢሰባዊ የሆነ ተግባር የሞተን ሰው ሪሳ መሬት ለመሬት ሲጓትቱ የተስተዋሉት በአፍሪካ ቀንድ ካሉ ሀገሮች ዉስጥ የተፈጽመው በወቅቱ መንግስት አልባ በነበረችው ሱማልያ ዉስጥ በአዉሮጳዊያን አቆጣጠር1993 በተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ የአሜሪካ ወታደር ላይ እና 2007 በአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪዎችኢትዪጵያ፤ኡጋንዳ እና ብሩንዲ ወታደሮች ላይ ነው። ይህም የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ከሀገራችን ለቀው ይውጡልን በሚሉ ቁጡ ሱማሌያውያን የተፈፀመ ነበር። የኛን ግን ለየት የሚያደርገዉ መንግስት ተብየዉ ወያኔ ድርጊቱ የተፈፀመ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን መሬት ለመሬት መጓተቱ ሳያበቃ በአደባባይ መስቀሉም ፍጹም አረመኔነቱን ያሳየ ተግባር ነው።
እነሱ ብቻ በተቆጣጠሩት የመገናኛ ብዙሀን የራሳቸውን የሽፍታነት ተግባር ለነጻነት ታጋዩ ምስኪን ገበሬ ይለጥፉለታል።አሽባሪ፣ጠባብ፣ሽፍታ፣ገንጣይ፣አስገንጣይ፣ጎጠኞ ወዘተ ይሉታል። ደርግም አኮ ፀረ ህዝብ ፣ፀረ አብዮት አያለ ነበር ሕዝብ ሲፈጅ የነበረው።
እነዚህምበተመሳሳዩ የተለያየ ታርጋ እየለጠፉ ሕዝቡን ጨረሱት :: እንዲህ ዓይነት ጭካኔ የተሞላበት ኢሰባዊ የሆነ ድርጊት እና የሥም ማጥፋት ዘመቻ በሕዝብ ላይ እስከ መቼ ሲፈፅመ ይኖራሉ?
ተማሪውን፣ገበሬወውን፣ሰራተኛውን፣ ከሕፃን አዋቂ ገደሉ፣አሰሩ፣አፈናቀሉ፣አሰደዱ፣የምንመካበትን የተፈጥሮ ሀብት መዘብሩ፣ትላልቅ መሬቶቻችን ወሰዱ፣ወንዞቻችንን መረዙ። ከዚህም አልፈዉ የምስኪኑን ገብሬ ሬሣ በራሱ ቀያ ላይ በወገኖቹ ፊት መሬት ለመሬት ጎተቱ እጅ እና እግሩን ጠፍንገዉ በአደባባይ ሰቀሉ ከዚህ በላይ ምን አይነት አረመናዊ ተግባር አለ? ከዚህ በላይ አምባገነናዊነትስ የት ይኖራል?
የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች ከተጨቆኑ ብሔር ፣በሔረሰብ እና ሕዝብ ጋር በመሆን በዚያች ሀገር ላይ ነፃነት ለማምጣት ከፍተኛ ሚና ሊጭወት ይችላል።
ሕዝብ ደግሞ በየትያውም ዘርፍ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት አካል ነው። ያለ ሕዝብ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እድገት እና ነፃነት የማይታሰብ ነው። የሕዝብ ድጋፍ የሌለው ልክ ምሰሶ የሌለው እቤት ነው። በተለያየ ግዜም ሕዝብ አምባገነን መንግስት ትብየው አካል ጋር እንዳሆነ አሳይቶል ወያኔም ሕዝብ አልባ አንደሆነ ይታወቃል።
እየደረሰብን ካለው ውርደት ለመዉጣት አና ነፃነታችን ለመጎናፀፍ እያንዳንዳችን ባለን አቅም እና ችሎታ የምናበረክተው አስተዋፆ ለትግሉአንድ ደረጃ መድረስ ለነፃነታችን ህውን መሆን ወሳኝነት አለው። ይህ በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ ድርጊት የመታገል የሁላችንም ግዴታ ነዉ።
ከዚህ በላይ ዉርደት የለም
ሁሉም የእግዛቤሔር ፍጥረቶች ሰዉ እና እንሰሳት ጭምሮ ምንም እንኳን ዓይነት እና ደረጃዉ የተለያየ ቢሆንም መብት አላቸው ።
በ 21 ክፍለ ዘመን አደጉ እና ሰለጠኑ የምንላቸው የዓለማችን ሀገሮች የእንሰሳት መብት ከሰው ልጅ መብት ባልተናነሰ ሁኔታ የሚከበርበት ደረጃ ላይ ተደርሶል። የነሱን መብት መጠበቅም ልክ እንደ አንድ የእድገት ደረጃ መቆጠር ከጀመረ ውሎ አድሮል። እነሱም ልክ እንደ አንደ ሰው ፍላጎት እና ስሜት አሏቸው ለምሳሌ ያህልም የህመም፣የደስታ፣የፍራቻ፣የብቸኝነት፣የስቃይ እና የእናት ፍቅር የመሳሰሉት ናችው። ለዚህም ነው ፍላጎታቸውን እና ስሜታቸውን የሚቃረን ተግባር መፈፀም የለበትም የሚሉ አያሌ የእንሰሳት መብት ተሞጋቾች የሚቃወሙት እና የሚታገሉት። መሀተመ ጋንዲ በአንድ ወቅት ¨የአንድ ሕዝብ ታላቅነት የሚለካው ወይም የምመዘነው ወይም የሚዳኝው ለእንሰሳት በሚሰጡት እንክብካቤ ነው ያሉት¨።
ዛሬ ግን ምስኪኑን ለፍቶ አደር የኦሮሞ ገበሬ ለነፃነት፣እኩልነት እና ፍትህ ብሎ የሚታገለውን እና ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት አልገዛም ያለውን ሰባዊ ከሆነ የፍጡር ደረጃ አወረዱት። ዛሬ ዓለም ለእንሰሳት ከምትሰጠው ክብር በታች አውርደውት ልክ እንዳልባሌ ነገር ቆጠሩት። ሰውን የሚያክል ክቡር ፍጡርን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉ በኃላ መሬት ለመሬት እየጎተቱ በአደባባይ መስቀላቸው ያቺ ሀገር መንግስት አልባ የተደራጁ የሽፍቶች ቡድን የምትገዛ መሆኖን ማሳያ ነው።
እነሱ ብቻ በተቆጣጠሩት የመገናኛ ብዙሀን የራሳቸውን የሽፍታነት ተግባር ለነጻነት ታጋዩ ምስኪን ገበሬ ይለጥፉለታል። አሽባሪ፣ጠባብ፣ሽፍታ፣ገንጣይ፣አስገንጣይ፣ጎጠኞ ወዘተ ይሉታል። ደርግም አኮ ፀረ ህዝብ ፣ፀረ አብዮት አያለ ነበር እኮ ሕዝብ ሲፈጅ የነበረው። እነዚህም በተመሳሳዩ የተለያየ ታርጋ እየለጠፉ ሕዝቡን ጨረሱት ::ታድያ እንዲት አንድ ጭብጥ ነቀዝ ወያኔ ማስወገድ አቅቶን እንዲህ ዓይነት ጭካኔ የተሞላበት ኢ-ሰባዊ የሆነ ድርጊት እና የሥም ማጥፋት ዘመቻ በሕዝባችን ላይ እስከ መቼ ሲፈፅመ ይኖራሉ? ነቀዝ ያልኩት ለመሳደብ ፈልጊም አይደለም ስድብ የኦሮሞ ባህልም አይደለምና። ቃሉን የተጠቀምኩት የወያኔን እና የነቀዝን ተመሳሳይነት እና አንድነት ለማሳየት ነው።
ሁለቱም ውስጥ ውስጡን እየበሉ ባዶ የሚያስቀሩ ተዋስያን ስለሆኑ ነው። በመሀከላችን የገቡትን እነዚን ተዋሲያን በመረባረብ ለአንዲ እና ለመጨረሻ ግዚ ማስወገድ ካልቻልን በታሪክ ተወቃሽ ከመሆን አናመልጥም ሌላም አካል ሊያስወግድልን አይመጣም። ¨surre jilbaa irraan dhumtee abbaatu warranata degaa Ijjollummaan dhuftee abbaatu tattafata¨ ይባላል።
ተማሪውን፣ገበሬወውን፣ሰራተኛውን፣ ከሕፃን አዋቂ ገደሉ፣አሰሩ፣አፈናቀሉ፣አሰደዱ፣የምንመካበትን የተፈጥሮ ሀብት መዘብሩ፣ትላልቅ መሬቶቻችን ወሰዱ፣ ወንዞቻችንን መረዙ። ከዚህም አልፈዉ የምስኪኑን ገብሬ ሬሣ በራሱ ቀያ ላይ በወገኖቹ ፊት መሬት ለመሬት ጎተቱ እጅ እና እግሩን ጠፍንገዉ ሰቀሉ ከዚህ በላይ ለኦሮሞ ሕዝብ ሞት ምን አለ? ከዚህ በላይ ወርደት ከወዲት ይመጣል?
የኦሮሞ ሕዝብ በዚያች ሀገር ላይ በብዛት ግንባር ቀደም ነው። ሕዝብ ደግሞ በየትያውም ዘርፍ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት አካል ነው። ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ሁለንተናዊ እድገት እና ነፃነት የማይታሰብ ነው። በተለያየ ግዜም ሕዝብ አምባገነን መንግስት ትብየው አካል ጋር እንዳሆነ አሳይቶል ወያኔም ሕዝብ አልባ አንደሆነ ይታወቃል። እየደረሰብን ካለው ውርደት ለመዉጣት አና ነፃነታችን ለመጎናፀፍ እያንዳንዳችን ባለን አቅም እና ችሎታ የምናበረክተው አስተዋፆ ለትግሉ አንድ ደረጃ መድረስ ለነፃነታችን ህውን መሆን ወሳኝነት አለው። ይህ በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ ድርጊት የመታገል የሁላችንም ግዴታ ነዉ።
ድል ለኦሮሞ ሕዝብ
No comments:
Post a Comment