Daniel እንደዘገበው:- አርብ እለት ከድሬዳዋ ተነስተው በደቡባዊ ኤርትራ አሰብ ዘልቀው የገቡት የወያኔው አየር ሃይል አብራሪዎች እና ቴክኒሺያኖች በደህና ሁኔታ ውስጥ ሲገኙ በኤርትራ የአየር ክልል የተቀበላቸው እና በ1987 አመተምህረት በወያኔ እና የደርግ መኮንኖች የሰለጠነው የሻእቢያ ኮማንዶ ጦር አጅቧቸው ወደ አስመራ ቤተመንግስት ከገቡ በኋላ በቤተ መንግስቱ ውስጥ ለሁለት ቀን በእንግዳ ማረፊያ ክፍል ውስጥ ቆይተው ወደ ሆቴል መዘዋወራቸውን ከአስመራ የተገኙ ምንጮች ጠቁመዋል::
በቤተ መንግስት ቆይታቸው አስፈላጊ ጥያቄዎች እና ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ከደምህት ጦር ጋር በመቀላቀል እየተገነባ ባለው ዘመናዊ አየር ሃይል ውስጥ አገልግሎት እንዲሰጡ የተጠየቁ መሆኑን ምንጮቹ ሲናገሩ አብራሪዎቹ ግን ወደ አውሮፓ ለመጓዝ ፍላጎቱ እንዳላቸው እና አውሮፓ ሆነው ትግሉን መርዳት እንደሚችሉ ሲናገሩ ተደምጠዋል::አብራሪዎቹ እጃቸውን የሰጡትም ሆነ የተቀላቀሉት ከኤርትራ መንግስት ጋር እንጂ ከሌላ አካል ጋር እንዳልሆነ ምንጮቹ አረጋግጠዋል::
ከደብረዘይት አየር ሃይል አከባቢ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በድሬዳዋ ያለው የአየር ሃይል ካምፕ ሃላፊዎች ላይ ከፍተኛ ግምገማ ተደርጓል::በዚህም መሰረት የሃገሪት የአየር ክልል ሳይቀር ከራዳር ውጪ ነው የሚል ጉዳይ ተነስቶ መነጋገሪያ እና መገማገሚያ ሆንዋል::እርስ በርስ መወነጃጀል እንኳን ባልተደፈረበት ግምገማ ላይ እያንዳንዱ መኮንን ሃላፊነቱን ወስዶ ዋጋ ሊከፊል ዪገባዋል ሲሉ ከፍተኛ አዛዦች በቁጣ ተናግረዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመጪዎቹ ሳምንት በሚካሄደው የግንቦት ሰባት እና የአርበኞች ግንባር ውህደት ላይ እስካሁን ወኪል ያላከው የአርበኞች ግንባር አንድ ሰው ከአውሮፓ አንድ ሰው ከአውስትራሊያ በመምረጥ ለእህደት ስብሰባው ማስትላለፉን ምንጮቹ ተናግረዋል::የተመረጡት አስመራ እንደደረሱ በውህደቱ ዙሪያ ንግግር እንደሚጀመር እና የፊርማው ውህደት እንደሚጸድቅ ኮሎኔል ፍጹምን ዋቢ ያደረጉ ምንጮች ጠቁመዋል::
No comments:
Post a Comment