Saturday, 11 October 2014
የኢህአዴግ ባለስልጣናት ስጋት ጨምሯል። ስብሰባ ማብዛት መፍትሄ አልሆነም
☞ «ተቃዋሚዎች ተንሰራርተዋል… ሕዝቡ እንዳይውጠን መጠንቀቅ አለብን»
☞ የተጀመረው ትግል ፍሬያማነቱ እየታየ ስለሆነ ተቃዋሚዎች እና ሕዝቡ በንቃት በጋራ መሳተፍ አለባቸው።
☞ የባለስልጣናቱ ተስፋ እየተመናመነ ስለሆነ ሕዝቡ ትግሉን ማጠናከር ይጠበቅበታል።
የወያኔ ባለስልጣናት በስልጣን የመቆየት ፍላጎታቸው ላይ የተደነቀረው የህዝብ አቤቱታ እና የተቃዋሚዎች መንሰራራት ስጋት እንደሆነባቸው ታውቋል። ህዝቡ በጎሪጥ እያየን ያለበት ሁኔታ ተቃዋሚዎች አንድ እርከን አንሰራርተው መታየታቸው እንዲሁም ዲያስፖራው ጥርሱን ነቅሶ በነቂስ እየተቃወማቸው እንደሆነ ከዚህም በተጨማሪ ስልጠና ብለው በጠሩበት ቦታ ላይ ሁሉ የደረሰባቸው ተቃውሞ ሕዝባዊ ጥያቄ እና አስተያየት እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ተወያይተዋል።
እንደ አዲሱ ለገሰ እምነት የተቃዋሚዎች መንሰራራት እና የህዝቡ ጥያቄ መፍትሄ ካልተፈለገለት በስተቀር እንደበሰበስን ማወቅ አለብን። በአሁን ወቅት እያየነው ያለነው ነገር ሕዝቡ ምን ያህል እንደተንገሸገሸ እና በጥያቄ ምልክት ውስጥ እንደከተተን ከስልጠናዎች የሚመጡ ሪፖርቶች ብቻ በቂ ናቸው። ከየቦታው በየጊዜው የሚሰበሰበው ሪፖርት ከታየ ከዚህ በበለጠ ምን ያህል በስብሰን ልንወድቅ እንደቀረብን ያሳያል። ብለዋል የኢህአዴግ የጀርባ አጥንቶች የሚባሉ አንጋፋ እና ታማኝ የሚባሉ ታጋዮች በተሰባሰቡበት ስብሰባ ውይይት ላይ። ህዝቡ ሊውጠን ይችላል ስልጠናዎች ላይ የታዩ ሂድቶች ይህንን አመላካች ናቸው። ብለዋል።
በተቃዋሚ ሃይሎች ውስጥ የመደብናቸው ሰዎቻችን ስጋት ላይ ናቸው። ምንም አይነት መረጃዎችን ይዘው አይመጡም ፍሬ ከርስኪ ወሬ ነው የሚያወሩት የሕወሓት ሰዎችን እንዳንመድብ ሕዝቡ በትግሬዎች ላይ ያለው ጥርጣሬ በፍጹም እንዳይተነፍስ ሆኗል። የምንከፍላቸው የተቃዋሚ አመራሮችን ከሃገር የሚወጡበት መንገድ ከማመቻቸት ውጪ ምንም ሲፈይዱ አላየንም። ከወጡ በኋላ የተለያዩ መረጃዎች እያፈተለኩ ያሉበት ሁኔት እየታየ ነው። የገዛናቸው ተቃዋሚዎች ሳይቀሩ በዘረፋ ተክነው ከሃገር ውጪ እየሸሹ ስለሆነ ሕዝቡ እንዳያበላሸን መጠንቀቅ አለብን ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ጸጋዬ በርሄ ተናግረዋል።
ወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣናቱ በውጥረት እና በስጋት ላይ መሆናቸውን የጠቆሙት ምንጮች ስርአቱ እንደበሰበሰ እና በጉልበት እንዲሁም በምእራባውያን ሃይል እየኖረ እንዳለ ተነጋግረውበታል። የምእራባውያን ድጋፍ ጥሩ ያለ ቢሆንም እያበሰበሰን እና እየገደለን ነው ያሉት ባለስልጣናት በፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ከፊል ገደብ እንዲጣል ተስማምተዋል። ከመጀመሪያው የትኛውን መብት ለፖለቲካ ድርጅቶች እንደሰጡ እንኳን ያልተረዱት ባለስልጣናት ፓርቲዎቹ እንዳይንቀሳቀሱ አድርገው ሳለ ከፊል ገደብ እንጥላለን ማለታቸው ባዶነታቸውን በገሃድ ያመላክታል ሲሉ ምንጮቹ ገልጸዋል።
ኢሕአዴግ እንደበሰበሰ በይፋ ያመኑት አቶ አዲሱ ለገሰ እና አቶ ጸጋዬ በርሄ በንግግራቸው ውስጥ ስለመጭው ጊዜ ከባድ ፍርሃት ይነበብባቸው ነበር ሲሉ የገለጹት ምንጮች ተቃዋሚ ፓርቲዎች የጀመሩትን ትግል አጠናክረው ከቀጠሉ ኢሕአዴግ ምንም አይነት ተስፋ እንደሌለው እና ምእራባውያንም ቢሆን የተቃዋሚዎችን ጥንካሬ እና በትግሉ መግፋት ካዩ ወደ ተቃዋሚው ጎራ የማይገለበጡበት አንዳችም ምክንያት የለም ሲሉ ምንጮቹ ኢህአዴግም ቢሆን ይህንን ጠንቅቆ ያውቀዋል ሲሉ አስረግጠው -
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment